የህብረት ስራ ማህበራት ሀገራችን ከያዘችው የልማትና የብልፅግና ጉዞ አንጻር እያበረከቱት የሚገኘው አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ኤጀንሲ ቀደም ሲል በተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት ዓይነቶች ተደራጅተው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚገኙ በመሆኑ፤
በዚህም መሠረት በአገልግሎት፤በማምረት እና በማምረት እና በአገልግሎት ዘርፍ በመደረጃት እራሳቸውን፤ ቤተሰባቸውን እና ሀገራቸውን እየጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም በማምረት እና አገልግሎት በመስጠት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የህብረት ስራ ማህበራት ሕግ እና መመሪያ አክብረው እንዲሰሩ ለማድረግ በተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት ዓይነቶችና የሙያ ዘርፎች በማደራጀት እንዲሁም መብታቸውን በመጠቀም ሕግን መሠረት አድርጎ መሥራት የሚያስችል ይህ የአደረጃጀት መመሪያ መዘጋጀት በማስፈለጉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (3) ተራ ፊደል (ሠ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡