የመመሪያ መለያ: 429/13
ቀን: ታህሳስ 20፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

ስደተኞች በስራ የሚሰማሩበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ የአሠራር መመሪያ ቁጥር 429/2013

አገራችን ለዘመናት ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ቀደምት ታሪክ ያላት አገር ስትሆን በአሁኑ ወቅትም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች አስጠልላ ትገኛለች፡፡

መንግሥት የስደተኞችን ጉዳይ አለማቀፋዊ ባህሪ ያለው መሆኑን በመረዳት በአለማችን እየሰፋ ያለውን የተፈናቀዮች እና ስደተኞች ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሁም ስደተኞች ለአንድ ሀገር ሸክም ሳይሆኑ እንደ ሀብት በመቁጠርም የልማት አጋር እንዲሆኑ ለማስቻል እና በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ አካባቢዎችም ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል መንግሥት ከዚህ በፊት በስራ ላይ የነበረውን የስደተኛ ሕግ በማሻሻል አዋጅ ቁጥር1110/2011 እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

አዋጁም ስደተኞችን ወደ ስራ ለማስገባት የተለያዩ የሀገሪቷ ህጎችን ያጣጠመ እንዲሆን ከመደረጉም ባሻገር ስደተኞች መንግሥት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ወደ ስራ የሚሰማሩበት እንዲሁም ለውጭ ሀገር ዜጎች የተፈቀዱ የስራ ዘርፎች ላይ ስደተኛው የስራ ፈቃድ በማውጣት መሥራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ይደነግጋል፡፡

በመሆኑም ይህ አዋጅ በሀገሪቷ ያልነበረውን አዲስ የስደተኞች አያያዝ በተሻለ ሁኔታ ያስቀመጠና በዚህ ሕግ ውስጥ ህጉን ለመፈፀም ስደተኞች ከወጭ ሀገር ዜጎች በተሸላ የሚስተናገዱበትን አሠራር የዘረጋ ቢሆንም አዋጁ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ስደተኛው በግል፣ በቅጥር እንዲሁም በጋራ ሊሰማሩባቸው በሚችሉ ስራዎች ላይ ግልፅ የሆነ የአሠራር ስርዓትና የሕግ ማዕቀፍ ባለማስቀመጡ ምክንያት አዋጁን ለማስፈጸም ወሳኝ የሆኑ የአጋር አካትን በማሳተፍ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት

FDRE Refugees and Returnees Service

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration