ለሞባይል ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ደንበኞች ቀደም ሲል የተመደበላቸው የሞባይል ስልክ ቁጥር በመያዝ ወደ ሌላ የቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተር የዛወር አማራጭ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በማኘቱ፤
በቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተሮች መካከል ወጥነት ያለው የሞባይል ቁጥር ማዘዋወር አሠራር እንዲኖር ቀልጣፋ እና ውጤታማ የቁጥጥር ስርዓት መኖር አስፈላጊነት በመገንዘብ፤
የሞባይል ቁጥር ማዘዋወር አገልግሎት አቅርቦትን በማከላዊነት የመምራት እና የማስተዳደር ኃላፊነት የሚኖረው ብሔራዊ የሞባይል ቁጥር ማዘዋወር ማጣሪያ ማዕከል ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፤
የደንበኞችን የተጠቃሚ መብቶች እና የዳታ ግላዊነት ማጠበቅ እና በሞባይል ቁጥር ማዘዋወር ሂደት ላይ ያላቸውን እርካታ መከታተል አስፈላጊነት በመገንዘብ፤
የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለሥልጣን በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጋ ቁጥር 1148/2011፣ አንቀጽ 6(2፣ 28(4)፣ 51(4) እና 54(2) መሠረት ይህንን የሞባይል ቁጥር ማዘዋወር መመርያ አውጥቷል፡፡