የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 553/99 ሲቋቋም ጥራታቸው የተረጋገጠ መሠረታዊ መድሀኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለተጠቃሚው ህበረተሰሰብ ለማቅረብ የተሰጠውን ሀገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችለው ቀልጣፋና ውጤታማ የግዥ አፈፃፀም አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣
ለሀገር ውስጥ አምራች ድርጅቶች የተለየ ማበረታቻ በመስጠት ለመድኃኒት እና ሕክምና መገልገያ ግዥ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ ማዳን አስፈላጊ በመሆኑ፣
የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በኤጀንሲው ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 553/99 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 5 በተሰጠው ሥልጣን ይህን የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያዎች ግዥ መመሪያ አውጥቷል፡፡