ኤጀንሲው የሰራተኞቹን ደኅንነት ለመጠበቅና ሊደርሱባቸው ከሚችሉ አደጋዎች የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ ሰራተኞቹን በተሰማሩበት የስራ መስክ ስራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ኤጀንሲው የደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች አፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል፡፡
በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ነሐሴ 2000 ዓ.ም በተላለፈው የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ጥናት፣ አፈቃቀድና አፈጻጸም በተቀመጠው መሠረት መስሪያ ቤቶች ካላቸው የስራ ፀባይ አንጻር የራሳቸው የሆነ የሙያ ጤንነትና ደኅንነት አጠባበቅ፣ የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች አፈቃቀድና አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ በዚህም መሠረት ኤጀንሲው የደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች አፈጻጸም መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡