በዓለም ዓቀፍ ንግድ በአንድ ሀገር የተመረቱ ምርቶችን ናሙና ወደ ሌላ ሀገር እንደ ማሳያ፣ ማስታወቂያ እና ከገዢ ደንበኞች ትእዛዝ ለማግኘት መላክ አስፈላጊ በመሆኑ፣
በሀገራችን እየሰፋ ከመጣው ኢንቨስትመንት ጋር ተያይዞ የምርት ናሙናዎች የመላክና የመቀበል ጥያቄ በዓይነትና በብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ፤
አምራች ላኪ ኢንዱስትሪዎች ከሚሊኳቸውም ሆነ ከሚቀበሏቸው ናሙናዎች ብዛት እና ዓይነት ጋር ተያይዞ ግልፅ፣ ቀልጣፋ እና ተገማች የሆነ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ማስጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ፣
የገንዘብ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 768/2004 አንቀጽ 32(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡