የመመሪያ መለያ: 152/2016
ቀን: መጋቢት 1፥ 2016 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት የአገልግሎትና ድጋፍ ማዕቀፍ መመሪያ ቁጥር 152 /2016

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአምራች ኢንዱስትሪ ንዑሳን ዘርፎች ላይ በማተኮር ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የድጋፍ ማዕቀፎችን በመቅረፅና ተግባራዊ በማድረግ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠርና እና ለሀገራችንና ለከተማችን ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት ማስቻሉ፤

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የዕድገት ደረጃና ፍላጎት መሠረት ያደረገ ድጋፍ በመስጠት፣ ጥራትና ምርታማነታቸውን በማሻሻል ተወዳዳሪና ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ በማስፈለጉ፣ በሚደረግላቸው ድጋፍ እና በሚያከናውኑት የምርታማነት እድገት መሠረት የላቀ የዕድገት ደረጃ ሽግግር እንዲያደርጉ ድጋፍ በማድረግ የማያቋርጥ የኢንዱስትሪ እድገት ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤

በተጨማሪም ጥራቱንና ደህንነቱን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት እንዲሰጡ አስፈላጊ በመሆኑ እና የላቀ የዕድገት ደረጃ ሽግግር እንዲያደርጉ በማስፈለጉ፤

ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የእድገት ደረጃ አወሳሰንና ሽግግር ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችንና በድጋፍ ማዕቀፍ አተገባበር ሂደት የሚታዩ ችግሮችን ግልጽና ተጠያቂነት ያለው አሠራር ሥርዓት በመዘርጋት መፍታት በማስፈለጉ፤

ጥራትና ምርታማነታቸው እንዲሳለጥ ለማድረግ የካይዘን አሠራርን በውጤታማነት ተግባራዊ ማድረግ ለኢንዱስትሪው የሚኖረውን ፋይዳ በመገንዘብ በአሠራር እና ሕግ ማዕቀፍ መደገፍ የሚገባ በመሆኑ፤

የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነትና ውጤታማነትን ለማሳደግ፣ ያለውን ውስን ሃብት በፍትሃዊነት፣ በአሳታፊነት እና በተወዳዳሪነት መንፈስ ግልፅ አሠራር በመዘርጋት መተግበር በማስፈለጉ፤

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 ዓ.ም አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration