የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የማኔጅመንት ኮሚቴ የተቋሙ ከፍተኛው አመራር ሲሆን ይህ አመራር በሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች የሚተላለፈው ውሳኔዎች ለተቋሙ የሥራ አፈፃፀም እንቅስቃሴ ቁልፍና ወሳኝ በመሆናቸው ኮሚቴው መመሪያን ተከትሎ ስብሰባዎችን ሊያከናውን እንደሚገባ ይታመናል፡፡ በዚሁ መሠረት የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የማኔጅመንት ፎረም ለሁለንተናዊ አሰራሩን ለማቀላጠፍ የአጀንዳ አመራረጥ፣ የአባላት ተሣትፎና የጊዜ አጠቃቀምና የዶክመንትና ማህደር አያያዝ የበለጠ ለማጠናከርና ፎረሙን ተቋማዊና ስታንዳርዳይዝ ለማድረግ ይህ የአሠራር ስርዓት መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡