ኢትዬጵያ ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች ላይ የተቀመጡ መብቶችን የሚፈፅም፤ለስደተኞች የተሻለ ከለላ የሚሰጥና ለችግሮቻቸው ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ የሚያስችል በዓለም ዓቀፍ መመዘኛዎች መሠረት የተቀረጸ ተቋም እንዲኖራት በማሰብ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይን ራሱን ችሎ በኤጀንሲ ደረጃ በአዋጅ 1097/2011 እንዲቋቋም ያተደረገ በመሆኑ በኤጀንሲው ቁመና አመራር ተመድቦ እየሰራ ያለ በመሆኑ፤
በሀገሪቱ ያለው የውጪ ምንዛሬ ወጥነት የሌለው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለ በመሆኑ፤
የኤጀንሲው አመራሮችና ሰራተኞች የውጪ ህክምናን የሚመለከቱ በስራ ላይ ያለው ሕግ ተግብራዊ በሚደረግበት ጊዜ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ለአገልግሎት ተጠቃሚው የተሻለ አሠራር በመዘርጋት የኤጀንሲውን ቁመና በሚያንፀባርቅ መልኩ የአመራሮችና ሰራተኞች የውጪ ህክምና መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ፤ የሚከተለው መመሪያ ወጥቷል፡፡