የመመሪያ መለያ: 765/2013
ቀን: ሐምሌ 1፥ 2005 ዓ.ም.
Language: Amharic

የቅርስ ምዝገባ መረጃ አያያዝና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 765/2013

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አንድ ወጥ የሆነ የምዝገባና የማእከላዊ የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የሀገራችን ቅርሶች ተመዝግበውና በዘመናዊ የቅርስ መረጃ አስተዳደር ቴክኖሎጂ ዘዴ ተካተው፤ አስፈላጊው እንክብካቤና ጥበቃ ተደርጎላቸው በተገቢው መንገድ ለትምህርት፣ ጥናትና ምርምር እንዲውሉ ማድረግ በማስፈለጉ፤

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ከመጣው ህገወጥ የቅርስ ዝውውር የሀገራችንን ቅርሶች ለመከላከል ያሉንን የቅርሶችን ብዛት አይነት ስርጭትና ተጋላጭነት ማወቅ በማስፈለጉ፤

በሀገሪቷ ለሚደረገው ዘላቂ ልማት ቅርሶች የራሳቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ለማድረግ የቅርስ ምዝገባ፣ መረጃና ቁጥጥር ዝርዝር መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

መሠረት ለቅርስ ምዝገባ’ ቁጥጥርና በቅርስ ጥናትና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 209/1992 አንቀጽ 46(2) እና በደንብ ቁጥር መረጃ ዘርፍ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ይህ መመሪያ የታንጀብልና የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶችን አጠናን፣ አመዘጋገብ፣ መረጃንና ቁጥጥርን ያካተተ ሲሆን፤ በተጨባጭ ያለውን አሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ በመፈተሽ፣ በሌሎች ሀገሮች ያሉትን ተሞክሮዎች በማየትና የስራ ሂደቱን በመገምገም የተዘጋጀ ነው፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

Ministry of Culture and Tourism

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration