ወጣቱ ትውልድ የነገው አገር ተረካቢ ዜጋ ከመሆኑም ባሻገር ለሀገሪቱ ፈጣን ልማትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ወሳኝ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ ወጣቱ የነገውን ሀገራዊ ኃላፊነትና አደራ በሚገባ ለመወጣት እንዲችል በመልካም አስተዳደግ ፣ በስነምግባር፤በትምህርትና ሥልጠና ተቀርጾ እውቀትና ክህሎት ያለው፤ ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ስብዕናው የተሟላ ፣ ለሀገርና ለሕዝብ ሁለንተናዊ እድገትና ልማት የሚጠቅም ብቁ ዜጋ ሊሆን ይገባል፡፡
ስለሆነም በኢትዮጵያ የተፋጠነ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ወጣቶች ያላቸውን የተጠናከረ ተሳትፎና ወደፊትም የሚኖራቸውን የጎላ ድርሻ ከግንዛቤ በማስገባት፣
– በስራ ላይ ሲሰማሩ ከተለያዩ የስራ ላይ አደጋዎችና የጤና ጉዳቶች እንዲጠበቁ ማድረግና እና
– ከባድና አካሊዊ ጉዲት ሊያስከትሉ ከሚችሉ አደገኛ ስራዎችና የስራ ሁኔታዎች መከላከል አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ
የኢፌድሪን ህገመንግሥት መሠረት ማድረግ ፣ ሀገሪቱ ከምትመራበት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፖሉሲ ጋር በማጣጣምና ከዓለም ዓቀፍ ስምምነቶችጋር በማገናዘብ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዲይ አዋጅ አፈፃፀምን ለማጏልበት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር በማድረግ ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡