የመመሪያ መለያ: 586/2013
ቀን: ጥር 1፥ 2006 ዓ.ም.
Language: Amharic

የደረጃ ዝግጅት ቴክኒክ ኮሚቴና የስራ ግብረ-ሃይል አባላት ማትጊያ ክፍያ መመሪያ ቁጥር 586/2013

በአገሪቱ ለሚገኙ አምራችና አገልግሎት ሰጭ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነትና ለአገር እድገት የደረጃ ዝግጅት ስራ ወሳኝ ሆኖ በመገኘቱ፤

ደረጃዎች የሚዘጋጁት ከተለያዩ ተቋማት በተወጣጡ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት መሆኑንና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ይህንን ሂደት በሴክሬታሪያትነት የሚመራና የሚያስተባብር መሆኑን በመገንዘብ፤

በዚህ የደረጃ ዝግጅት ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ሙያዊ አስተዋፅኦ ወሳኝነት፣ ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪነት የሚሰሩት መሆኑንና ከእውቀት ከክሎትና ልምድ በተጨማሪ ትኩረትና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት፤

በአንፃሩ ባለሙያዎች ከየመጡበት ተቋም ለዚህ ሥራ ክፍያ የሚፈጸምበት አሠራርና ዝግጁነት ገና ያልተፈጠረ በመሆኑ፣ ይህን ክፍተት ለመሙላት መንግሥት የማትጊያ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልገው በመረዳትና ቀደም ብሎ ይሰራበት የነበረው መመሪያ አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ እንዲጣጣም ማድረግ በማስፈለጉ፤

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 193/2003 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 4 እና በአንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት ይህን የማትጊያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ

Institute of Ethiopian Standard

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration