የመመሪያ መለያ: 703/2013
ቀን: ጥር 1፥ 2007 ዓ.ም.
Language: Amharic

የመሬት ይዞታ ምዝገባ ክፍያ ቀመር መመሪያ ቁጥር 703/2013

በሃገሪቱ ያሉ ከተሞች ያላቸውን መሬት መጠን፣ በማንና እንዴት እንደተያዘ እና በይዞታዎቹ ላይ ያለን መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ ትክክለኛና ወቅታዊ ሆኖ ስለይዞታው በሰነድና በመስክ ያለውን ሁኔታ በመለየት በይዞታዎቹ ላይ የመጠቀም መብት ያላቸውን ባለይዞታዎች ዋስትና በማረጋገጥ የንብረት ዝውውር የተቀላጠፈ ለማድረግ መንግሥት የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ተቋም ያቋቋመ እንደመሆኑ እና የከተሞች የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ አገልግሎት ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ እና ተደራሽ በማድረግ ማንኛውም ሰው በመሬት ይዞታው ላይ በህጋዊ መንገድ ለሚያሰፍረው የማይንቀሳቀስ ንብረት ዕውቅና በመስጠት የህዝቡን በመሬት ይዞታው የመጠቀም እና በይዞታው ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም ግልጸኝነት ተጠያቂነት የሰፈነበት አሠራር በመፍጠር የዜጎችን የመንግሥትንና የግሉን ዘርፍ ጥቅም ማስጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤

የመሬት አስተዳደር ሥርዓታችንን ወደ ተሻለ አፈፃፀም ሊያደርስ የሚችል ከነፃ ገበያ ልውውጥ ጋር የተጣጣመ የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት በነፃ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ ላይ አስተዋፅኦ እንዲኖረው ለማድረግ እየተሞከረ ነው፡ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት እውን ለማድረግ የምዝገባ ተቋም የተለያዩ አገልግሎት እንደሚሰጥ ታሳቢ በማድረግ ለዚህም አገልግሎት በተለይ በቁራሽ መሬቱ ላይ የሚከናወነው የማረጋገጥና ምዝገባ ሥራ በተለያየ ጊዜና በተበጣጠሰ መልኩ ሲቀርቡ የአገልግሎት ክፍያ መተመን በማስፈለጉ በከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818/2006 አንቀጽ 52(2) መሠረት ይህ የመሬት ይዞታ ምዝገባ ክፍያ ቀመር የተዘጋጀ ሲሆን የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 45/2007 አካል ሆኖ በሥራ ላይ ይውላል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration