የመንግሥት መ/ቤቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ በጋራ ቅጥር ለማገልገል ፍላጎት ያላቸውን ሠራተኞች ለማሰማራት በተለይም ባላቸው ልዩ እውቀትና ክህሎት በማስተማር ወይም በምርምር ስራቸው አርአያነት ባለው፣ በግል ሰብእናቸው የታወቁ፣ የስራ ተሞክሮ፣ እውቀት እና የስራ ልምዳቸውን በማካፈል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል፣ በመንግሥት መስሪያ ቤት ውስጥ በተመዘነና በተፈቀደ ወይም በሙያ እድገት መሰላል ስራ መደብ ላይ ሠራተኛን በጋራ ለመቅጠርና ለማስተዳደር የሚያስችል ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣ በፌዴራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 23 ንዑስ አንቀጽ (2) እና አንቀጽ 97 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡