የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ኤክስፖርት መር በሆነው የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ውስጥ ብቁ ተወዳዳሪ ሆነው ለልማቱ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ይጠበቃል፡፡ እንዲያውም አሁን ባለው የአገሪቱ ኢንዱስትሪ ደረጃ ስትራቴጂውን ለማስፈጸም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ የልማት ድርጅቶች ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ካላቸው አቅም አንፃር የመሪነት ሚና መጫወት አለባቸው፡፡
በተጨማሪም በልማት ስትራቴጅው የተቀመጠውን ዓላማ ለማሣካት ከግል ባስሀብት ጋር አብሮ መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡ የልማት ድርጅቶች ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ቢፈለገም አብዛኞቹ ከማኔጅመንት ከአሠራር፣ ከቴክኖሎጂ እና ከካፒታል በተያያዙ ችግሮች ምክንያት ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ አዳግቷቸዋል፡፡ እነዚህን ድርጅቶች ወደ ግል ባለቤትነት በሽያጭ በአጭር ጊዜ ለማዞር የተደረገው እንቅስቃሴም በተጠበቀው ፍጥነት ሊከናወን አለተቻለም:: ስለሆነም የልማት ስትራቴጂውን ለማሳካት እና የልማት ድርጅቶቹን የብቃት ችግር በወቅቱ ለመቅረፍ አቅም ካለው የግል ባለሃብት ጋር በጋራ ልማት ትብብር በቅንጅት በመሥራት በኤክስፖርት የተቀኙ ተወዳዳሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በአጭር ጊዜ ማፍራት ይቻላል ተብሎ ይታመናል::
በሌላ በኩል ገቢ ምርቶችን የመተካት ሚና ያላቸው ድርጅቶችም ቢሆኑ ከአጋር ጋር በመሥራት ተወዳዳሪነታቸውንና የገበያ አድማሣቸውን እንዲያሠፉ ማድረግ አግባብ ነው፡፡ በመሆኑም የጋራ ልማቱን (Joint Investment) ሥርዓት ባለው መንገድ መምራት መመሪያ ማዘጋጀቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ ይህ መመሪያ በጋራ ልማት ከኮንትራት በፊት ቅድመ ዝግጅቶችንዶ በኮንትራክት ወቅት የሚታዩ ጉዳዮችንና ከኮንትራክት በኋሳ ያሱ የአፈፃፀምና የክትትል ሥራዎችን ያካተተ ነው፡፡ የጋራ ስማት ማስፈፀሚያ መመሪያ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባስሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 277/94 መሠረት ሕጋዊ ሰውነት አግኘቶ ሲቋቋም በአንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 2 እና በኢንቨስትመንት አዋጅ 280/94 አንቀጽ 7 ከተሰጠው ሥልጣን መንጭቶ የተዘጋጀ ነው፡፡