ሥራ ፈላጊ የከተማ ነዋሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሆኑ ይህን የሰው ኃብት በተገቢው የሕግ ማዕቀፎች በመምራት ሥራ ውጤታማ ማድረግ በማስፈለጉ፤ ላይማሰማራትና
ሥራ ፈላጊዎችንና ክፍት የሥራ ቦታዎችን መመዝገብ የሥራ ፈላጊ የከተማችን ነዋሪ እንግልት ለመቀነስና ለሁሉም ዜጎች እኩል የሥራ ዕድል የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና አሠሪም ለሥራው ብቁ የሆነ ሠራተኛ እንዲያገኝ እገዛ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የሥራ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡