የመመሪያ መለያ: 78/2014
ቀን: ጥቅምት 1፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት መመሪያ ቁጥር 78/2014

በሀገራችን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለበርካታ ዓመታት ስር ሰዶ የቆየ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንትርፕራይዝ ልማት ቢሮ የከተማችን ሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚ እያደረገ የመጣ መሆኑ እና ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንትርፕራይዞች በከተማችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚየዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና እንዳላችው ይታወቃል፡፡

ለዘርፉ ልማት ትኩረት በመስጠት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የልማት ፖሊሲና ስትራተጂ ላይ ተመስርቶ የራሱ ፕሮግራምና ድጋፍ ፓኬጅ ተዘጋጅቶ በተመረጡ ዕድገት ተኮር ዘርፎች ላይ በማተኮር ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ መስጠት ተችሏል። ስለሆነም ልማቱን ለማፋጠን የተከናወኑ ተግባራት በአብዛኛው በመንግሥት ድጋፍ ላይ የተመሠረቱ ሲሆን በኢንተርፕራይዞች የተጠናከረና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ተቋም ከመፍጠር አኳያ ሰፊ ክፍተት ታይቷል፡፡

ኢንተርፕራይዞች በዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባለመደራጀታቸው የጥሬ ዕቃ አቅርቦት፤ የማሽነሪ አቅርቦት የዕውቀት፣ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የገበያና የምርት ትስስር አገልግሎት በአንድነት ለማከናወን እና ወጪን በመቀነስ አቅርቦታቸውን በመጨመር የምርት ጥራትና ምርታማነት ተወዳዳሪ መሆን ባለመቻሉ፤ በከተማችን የሚገኙ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ችግራቸውን በጋራ ለመፍታት፤ መልካም ዕድሎችን በጋራ ለመጠቀም፤

እንዲሁም መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር የኢንተርፕራይዞች የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እንዲደራጅ በማድረግ አሁን የተገኙትን ጅምር ውጤቶች ይበልጥ ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (3) (ሠ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን

Job Creation Commission

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration