የአገራችን የቱሪዝም ኢንደስትሪ ለአገራችን የገጽታ ግንባታ እና ለኢኮኖሚው ሊያበረክት የሚችለውን አስተዋፅዖ ለማሳደግ እንዲቻል ለቱሪስት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ቱሪስቶች ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታ በግልጽ መደንገ በማስፈለጉ፣
ቱሪስቶች በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ በሚያስገቧቸው ዕቃዎች ላይ ውጤታማ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ግልጽና ወጥ አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 71 (1) እና 180 (2)መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡