የኤክሳይዝ ታክስ በትክክል መሰብሰቡን ለማረጋገጥ፣ ህገወጥ ንግድን ለመከላከል፤ እና የሕዝብ ጤና እና ደኅንነትን ለመጠበቅ የሚያስችል ዲጂታል እና አካላዊ የኤክሳይዝ ቴምብርን ስራ ላይ ማዋል ከፍተኛ እገዛ የሚኖረው በመሆኑ፣
የኤክሳይዝ ታክስ አስተዳደር ሥርዓትን ለማዘመን፤የኤክሳይዝ ታክስ ህጎች እንዲከበሩ ለማድረግ፤
ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲሁም የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን እቃዎች ምርት እና ስርጭት ለመከታተል የሚያስችል የኤክሳይዝ ቴምብር አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
የገንዘብ ሚኒስቴር በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2018 (በተሻሻለው) አንቀጽ 29 እና 42 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።