የመመሪያ መለያ: 527/2013
ቀን: ጥር 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ምኅንድስና ባለሙያዎች እና ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 527/2013

የብረታ ብረትና የምህንድስና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሙያን ማልማትና ማሳደግ ለሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት መጎልበት ብሎም ለምጣኔ ሀብት ዕድገት መሠረታዊ በመሆኑ፣

ለብረታ ብረት እና ለምህንድስና ኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና መልማት የምህንድስናና የመሰል የሙያ መስኮች እውቀትና ክህሎት መገኘትና ተግባራዊ መሆን የግድ በመሆኑ፣

የግሉ ዘርፍ በኢንዱስትሪው መስክ ቁልፍ ባለድርሻ በመሆኑ እና የዚሁ የግሉ ዘርፍ አቅም ማለትም የሰው ሃይል(የባለሙያ)፣ የመሳሪያ እና የተቋሙን አጠቃላይ አቅም በቅድሚያ በማወቅ ያለበትን ደረጃ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፣

መንግሥት በማምረት ሥራ ላይ የሚሰማሩ ባለሙያዎች ፣ አማካሪዎችና ሥራ ተቋራጮች በሚሰሩት ሥራ የደህነነት ፣ የጥራትንና የውጤታማነት መስፈርትን እንዲያሟሉ ብሎም የሕዝቡን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዱ የብቃት ማረጋገጫ የምዘና ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፤የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 47/1989ዓ/ም አንቀጽ /6/7፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 256/1994ዓ/ም አንቀጽ 5/2/፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ለማሻሻል የወጣአዋጅ ቁጥር 411/1996 አንቀጽ 2/3/፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 691//2003 አንቀጽ 20/2/ ፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 21/18/ እና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 1097//2011 አንቀጽ 19/2/ መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

Ministry of Industry

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration