የስራ ሂደቱን የውስጥ አሠራር በሕግና መመሪያ መምራት የአሠራር ግልጽነትን፤ፍትሃዊነትንና ተጠያቂነትን ከማስፈኑ በተጨማሪ በስራ ሂደቱ ውስጥ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች በሚያከናውኗቸው ተግባራት ላይ ለደንበኞች ፈጣን ውሳኔ መስጠት የሚያስችላቸው መሆኑ ግልጽና አስፈላጊም ነው፡፡ ስለሆነም በስራ ሂደቱ ልዩ ትኩረት ከሚያስፈልጋቸውና ግልጽ የውስጥ አሠራር የሚጠይቁ ከስራ ክትትልና ሪፖርት፤ ከፋይሎችና መረጃ አያያዝ፤ ከውሳኔ አሰጣጥና ከሙያ ስነምግባር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የውስጥ አሠራር መመሪያ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የአሠራር መመሪያ እንዲዘጋጅና ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡