በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ጠንካራና ዘመናዊ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትን በመዘርጋት የሂደቱን ውጤታማነት በተገቢው ሁኔታ ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፣
የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ዓላማና ግቦችን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የውስጥ ኦዲት አስተዳደሩን ቁጥጥሩን እና የኮርፖሬት አስተዳደሩን ሂደትና ውጤታማነት በመገምገም ቀጣይነት ባለው አሠራር የማሻሻያ ሀሳብ እንዲሰጥ የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣
የውስጥ ኦዲት ነፃ፣ ገለልተኛና ሚዛናዊ ሆኖ በነፃ ህሊና ላይ ተመስርቶ ተግባራቱን የሚያከናውን፣ የምክር አገልግሎት የሚሰጥ፣ ተጨማሪ እሴት (Value Add) የሚያስገኝና የድርጅቶችን የሥራ አፈፃፀም የሚደግፍ እንዲሆን ማድረግ በማስፈላጉ፣
የውስጥ ኦዲት የመረጃዎች አስተማማኝነትና ትክክለኛነት፣ የፖሊሲዎች፣ ዕቅዶች፣ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ተግባራዊነት እንዲሁም የልማት ድርጅቶችን የሀብትና ንብረት አጠቃቀምና ጥበቃን ተገቢነት በማረጋገጥ አጋዥ ኃይል እንዲሆን ለማድረግ በማስፈለጉ፤
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኤጀንሲውን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው ደንብ ቁጥር 445/2011 አንቀጽ (5) ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡