የመመሪያ መለያ: 100/2014
ቀን: መጋቢት 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ በውክልና ለማስመርመር የወጣ መመሪያ ቁጥር 100/2014

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሺዎች የሚቆጠሩ ህብረት ሥራ ማኅበራት ሲኖሩ እነዚህም ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሰፊውን እና በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ኅብረተሰብ በማቀፍ ለከተማችን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡

ኀብረት ሥራ ማኀበራቱም አገልግሎት ሰጪ እንደመሆናቸው መጠን የሚያከናውኑት ተግባር በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እየተመዘነ አዋጭ እና ለአባላት ጠቀሜታ የሚሰጡ ተቋማት መሆናቸውን ለመለካት እንዲቻል እና ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውን የሂሣብ አያያዝ ሥርዓት እንዲከተሉ እንዲሁም በሌሎች ተቋማት ዘንድ አመኔታ ለማሳደር እንዲችሉ ማድረግ የከተማው ህብረት ስራ ኤጀንሲ ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡

በአዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት አግባብ ያለው ባለሥልጣን ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የማንኛውንም ኀብረት ሥራ ማህበር ሂሣብ ራሱ ወይም እሱ በሚወክለው ሰው መመርመር እንዳለበት ተደንግጓል፡፡

ነገር ግን በከተማችን ነባራዊ ሁኔታ የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው በርካታ ዜጎች በአማራጭነት በህብረት ስራ ማህበር የመደራጀት ፍላጎት በማሳየታቸው ፤ ኀብረት ሥራ ማኀበራት በደረጃ፤ በአይነትና በቁጥር እያደጉ በመምጣታቸው ፤ የሕዝብ ተቋማትም በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲተዳደሩ በመደረጉ አስቀድሞ ይደረግ እንደነበረው አግባብ ባለው ባለሥልጣን ብቻ ይህን አገልግሎት ለማዳረስ አልተቻለም፡፡

ስለዚህ የኀብረት ሥራ ማኀበራት ሂሳብ በአዋጁ መሠረት ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መመርመር እንዲቻል በውክልና ማስመርመር የሚቻልበትን አሠራር መቀየስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 76 ቁጥር 3 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የኀብረት ሥራ ማኀበራትን ሂሣብ በውክልና ለማስመርመር የሚያስችል ቁጥር 5/2010 መመሪያን አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ

Addis Ababa City Administration Cooperative Agency

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration