የመመሪያ መለያ: 35/2013
ቀን: ጥቅምት 1፥ 2004 ዓ.ም.
Language: Amharic

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የኃይማኖት ተቋማት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለመስጠት የወጣ የአሰራር መመሪያ ቁጥር 35/2013

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከመሬት ጋር ከተያያዙት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንዱና ዋነኛው አብዛኛው ይዞታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ የሌለው መሆኑና በተጨማሪም በመሬት ላይ የሚደረገውን ህገወጥ ተግባር ለመከላከል ህጋዊ የሆነውና በህገወጥ የተያዘው ይዞታ ተቀላቅሎ መገኘቱ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት የሚያግዙ መመሪያዎችና የአሠራር ማኑዋሎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ናቸው። ሆኖም እስከአሁን የተዘጋጁት መመሪያዎችና ማኑዋሎች ከኃይማኖት ተቋማት ይዞታዎች ውጭ በተያዙት ይዞታዎች መስተንግዶ ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው በኃይማኖት ተቋማት በተለያየ ጊዜ በልዩ ልዩ መንገዶች ለተያዙት ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሳይቻል ቀርቷል፡፡

ስለሆነም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ለሌላቸውና እስከ መሰከረም 9/1998 ዓ.ም ለተያዙ የኃይማኖት ተቋማት ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አዘጋጅቶ ለመስጠትና ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት የሚያግዙ መመሪያዎችና የአሠራር ማኑዋሎች አዘጋጅቶ ተግባራዊ በማድረግ የኃይማኖት ተቋማት ይዞታዎችን ከተቋማቱ እገልግሎት እንጻር ማስተናገድ ተገቢ በመሆኑ ለዚሁ የሚያግዝ እራሱን የቻለ አሠራር ቀየሶ ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤

በከተማ ዉስጥ የአምልኮና እና የዘላቂ ማረፊያዎች ያለሕጋዊ ፈቃድ እየተያዘ መሆናቸው በሕዝብ ጤና እና ኑሮ በከተማው አጠቃላይ እድገት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር በመቅረፍ የቦታዎቹ አጠቃቀምና አስተዳደር ዘመናዊ እና ተገቢውን ደረጃ ያሟላ እንዲሆን በማድረግ ሕጋዊ ሥርዓት ማስያዝ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የከተማው አስተዳደር ኃይማኖቶችን ሁሉ በእኩል ደረጃ በከተማዉ መዋቅራዊ ኘላን በተመለከተው የማኀበራዊ መሠረተ ልማት አውታር፣ የአምልኮና የዘላቂ ማረፊያ አገልግሎት ቦታዎችን ስርጭት በመከተል አገልግሎቶችን ማስተዳደር የሚገባዉ በመሆኑ፤

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ

City Government of Addis Ababa Land Development and Management Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration