የመመሪያ መለያ: 89/2013
ቀን: ኅዳር 18፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

በውጭ አገር ለሥራ የሚሰማሩ ዜጐችን የመድን ሽፋን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 89/2013

ይህን መመሪያ ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 923/2008 አንቊዕ 62 ላይ ለሥራ ወደ ውጭ አገር ለሚሄድ ማንኛውም ሠራተኛ አሰሪው የሕይወትና የአካል ጉዳት ካሳ የመድህን ሽፋን በአገር ውስጥ የመግባት ግዴታ እንዳለበት በመደንገጉ ለሥራ ወደ ውጪ አገር የሚሄዱ ዜጎች በስራ ላይ ሊደርስባቸው ለሚችል ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና አካላዊ ጉዳት እና ጥቃት ተገቢው ጥበቃ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ለስራ ወደ ውጭ አገር ለሚሄድ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሠራተኛ አሰሪው በአገር ውስጥ የሕይወትና የአካል ጉዳት ካሳ ኢንሹራንስ ለመግባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ በመድህን ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 መሠረት ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ በማውጣት እየሰሩ የሚገኙ የኢንሹራንስ ድርጅቶች ግልጽነትና ፍትሃዊነትን በተከተለ አግባብ ተሳታፊ የሚሆኑበትን አሠራር ለመዘርጋት ይህ የአፈጻጸም መመሪያ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

Ministry of Labor and Social Affairs

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration