የመመሪያ መለያ: 918/2014
ቀን: ሐምሌ 1፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የተቋማት፣ የአመራር እና የአካዳሚክ ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ቁጥር 918/2014

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሥራ አፈጻጸም የሚመዘንበት ወጥነት ያለው የአፈጻጸም መመሪያ በማስፈለጉ፣

የከፍተኛ ትምህርት አመራሮች፣ የአካዳሚክና የምርምር ሠራተኞች፣ የሥራ አፈጻጸም ምዘና አተገባበር እንደየተቋማቱ የተልዕኮ ስኬት ላይ ተመስርቶ ወጥነት ባለው የአሠራር ሥርዓት ማስተግበር በማስፈለጉ፣

በነባሩ የመገምገሚያ መስፈርት ላይ እንደ የምርምር ሥራና የማኅበረሰብ አገልግሎት ጉዳዮች ዙሪያ የታዩ ውስንነቶችን በማስቀረት የአፈጻጸም ምዘና መመሪያው ከከፍተኛ ትምህርት ልማት ሴክተር ማሻሻያ ፕሮግራሞች ጋር እንዲጣጣም በማስፈለጉ፣

በከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት ውስጥ የተቋማት እና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሥርዓት በየደረጃው ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት አሠራርን የተከተለ ማድረግ በማስፈለጉ፣

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የሃብት አጠቃቀም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመፈፀም ብቃት በማጎልበት ውጤታማ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፣

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ አመራር እና የአካዳሚክ ሠራተኞች በተሰጣቸው የተልዕኮ አፈጻጸም ውጤት ላይ በመመስረት የዕውቅናና ማበረታቻ የሚያገኙበትን ስርዓት በማጠናከር፣ የአቅመ-ግንባታ ሥልጠና የሚሰጥበት እና የዕርምት እርምጃ የሚወሰድበት ሥርዓት በመዘርጋት የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፣

በመሆኑም በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 86(5) እና የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 34(2) መሠረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የትምህርት ሚኒስቴር

Ministry of Education

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration