በዓለም ላይ እንዲሁም በሀገራችን የመንገድ ትራፊክ አደጋ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፡ ለዚህም አደጋ ዋና መንስኤ የተሽከርካሪ ፍጥነት እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶችና ምርምሮች ያሳያሉ፡ በዚሁ መሠረት የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ በመግጠም የተሽከርካሪዎች ፍጥነት በመገደብ አደጋውን መቀነስ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም ባለስልጣነ በአዋጅ ቁጥር 468/1997 የተሰጡት ተግባራትና ኃላፊነቶች ውስጥ በአንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 3/ሐ/ የትራፊክ አመራሩ ውጤታማ የሚሆንበትን ስልት በመቀየስና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት ከመደንገግና የትራፊክ አመራሩን ውጤታማ ለማድረግ በፍጥነት ምክንያት የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ ባለስልጣኑ የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣ የደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡