የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚገለገልባቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ በወቅቱና ደህንነቱ በተጠበቀ አኳኋን መፈጸም አስፈላጊ በመሆኑ፣
ኤጀንሲው ሀገራዊ በሆኑ የኢንፎርሜሽን ኔትወርክና የኢንፎርሜሽን ደኅንነት ሥራዎች ላይ የሚሰራ ተቋም በመሆኑ ለስራው የሚገለገልባቸው በአብዛኛው ከውጭ ሀገር የገሚዙ ዕቃዎች በተለየ ጥንቃቄ ማገዛት ስለአለባቸው እና እንደ ግብአት የሚጠቀምባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች የቴክኖሎጂ ምንጫቸው፣ የጥራት ደረጃቸው ሞዴልና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በግዥ ሥርዓቱ ምክንያት ለሌላ አካል መተላለፍ ሳይኖርባቸው ሚጠራዊነታቸው ተጠበቆ ግዥዎችን መፈፀም አስፈላጊ በመሆኑ፣
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የግዥ ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 3/2/ሀ/ እና 78/2/ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 8 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡