የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተሰጠውን ኃሊፊነት ከግብ ለማድረስ የሚገለገልባቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ በወቅቱና ደህንነቱ በተጠበቀ አኳኋን መፈፀም ያለበት በመሆኑ፣
ኤጀንሲው የደኅንነት ተቋም ከመሆኑ አንፃር ለሥራ የሚገለገልባቸውን በአብዛኛው ከውጭ አገር የሚገዙ ዕቃዎች ሚስጥራዊነታቸው ተጠብቆ በተለየ ጥንቃቄ መገዛት ስላለባቸው፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 3 ቁጥር 2(ሀ) ለሚኒስትሩ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡