የኤርትራ መንግሥት በከፈተብን ጦርነት ምክንያት ከአገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩኤርትራዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸውን ንብረት ማግኘትና ማልማት እንዲችሉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 7 ቀን 2001 ዓ.ም መመሪያ ያወጣ በመሆኑ፤ ይህንኑ መመሪያ ለመተግበር የሚያስችል ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ በመመ ሪያው አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 6 መሠረት ከዚህ የሚከ ተለው የአፈፃፀም መመሪያ ወጥቷል።