የመመሪያ መለያ: 969/2015
ቀን: ግንቦት 23፥ 2015 ዓ.ም.
Language: Amharic

ተጎጂ ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 969/2015

በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 መሠረት ተጎጂ የፍልሰት ተመላሾች ተገቢ የጤና፣ የማኅበራዊ አገልግሎት፣ የሕግና ሥነ-ልቦና ምክርና ድጋፍ፣ ጊዜያዊ መጠለያ፣ የኢኮኖሚ ድጋፍ እና መሰል አገልግሎቶችን እንደሚያገኙ የተደነገገ በመሆኑ፤

በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ተለያዩ ሀገራት ፈልሰው የተለያዩ ጉዳቶችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽሞባቸውና ተጋልጠው እየተመለሱ በመሆኑና ከጉዳታቸው አገግመው ወደማህበረሰቡ በዘላቂነት ተመልሰው እንዲቀላቀሉ የማኅበራዊ፤ የስነ ልቦና እና የኢኮኖሚ ድጋፎች እንዲያገኙ ማስቻል አስፈላጊ በመሆኑ፤

በተጎጂ ከፍልሰት ተመላሾች መልሶ ማቋቋም ሂደት ተሳታፊ የሆኑ ባለድርሻ አካላት የሚኖራቸውን ሚና መግለጽ፤ በመካከላቸው ስለሚኖረው ቅንጅታዊ አሠራር መወሰን እና ወጥነት ያለው የመረጃ አያያዝ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

በተጎጂ የፍልሰት ተመላሾች መልሶ ማቋቋም ድጋፍ ማዕቀፍ የሚሸፈኑ ጉዳዮችን እና የድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓቱን በዝርዝር በመወሰን መልሶ ማቋቋሙን ፍትሀዊ፣ ተደራሽ እና ወጥነት ባለው መልኩ ማከናወን በማስፈለጉ፤

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፍትሕ ሚኒስቴር በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀጽ 46(2) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የፍትህ ሚኒስቴር

Ministry of Justice

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration