የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የተሰጠውን ግብር እና ታክስ የመሰብሰብ ኃላፊነት በተሟላ መልኩ በመወጣት ለከተማዋ ዕድገትና ልማት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን ለተከታታይ ሁለት ዓመታትም በገቢ አሰባሰቡ የቢሮው ሠራተኞችና አመራሮች ባደረጉት ርብርብ አዳጊ የሆነ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኝ በመሆኑ፤
የተቋሙን የገቢ አሰባሰብ ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ የተደረገውን ጥረት እና የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛ መሆኑን መረዳት በመቻሉ እና ለዚህ ውጤት መሳካት አስተዋጽኦ ለነበራቸው የቢሮው አመራሮች እና ሰራተኞች በተቋሙ የተዘረጋን የማትጊያ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የገቢዎች ቢሮ የሠራተኞች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 99/2010 አንቀጽ 47 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የአፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል፡፡