የመመሪያ መለያ: 582/2013
ቀን: ጥር 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል የትምህርትና ስልጠና ዕድል አሰጣጥና አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 582/2013

ለአንድ ተቋም ወይም ድርጅት የቆመለትን ዓላማ እና ተልዕኮ ማሳካት የሚችልበት ትልቁ ሃብትና መሣሪያ ሰብዓዊ ሃብት ነው፡፡ በዓለም ላይ ያለው ተጨባጭ ልምድ ድርጅቶች ወይም ተቋማት የሰው ሃይል በቅጥር ወደ ሥራ ማሰማራት ብቻ ሳይሆን በሥራ ላይ የማብቃት ሠራ መሥራት እንደሚገባቸው ነው:: በዚህም የተቋም ወይም ድርጅት የሰው ኃይል ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የትምህርትና ሥልጠና የሚመራበት ኘሮግራምና ሥርዓት በመቅረጽ እንዲመራ ማድረግ ይገባል፡፡ ለዚህም እንደተቋሙ/ድርጅት የአደረጃጀት ባህሪይና ፍላጎት የውስጥ አሠራርመመሪያ በማዘጋጀት ሠራተኞች በዕቅድ ላይ የተመሠረተ እና ፍትሃዊ ከአጫጭርዕስከ ረዥም ጊዜ እንዲሁም ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ አገር የትምህርትና ሥልጠና ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ፡፡

የመንግሥት ሰራተኞች አዋጅም እንዳስቀመጠው የመንግሥት ሠራተኞች እንዲሰለጥኑ የሚደረገው በተመደቡበት ሥራ የተሻለ የሥራ ውጤት ለማስመዝገበና ለበለጠ የሥራ ኃላፊነት እንዲበቁ ለማዘጋጀት ነው፡፡ በመሆኑም እንደመንግሥት መሥሪያ ቤት በታህሳስ 7/2010 በወጣው የፌዴራል መንግሥት ሠራተኛ አዋጅ መሠረት እያንዳንዱ የመንግሥት መስሪያ ቤት ለመስሪያ ቤቱና ለሠራተኛው የሚያስፈልገውን የማልማት ሥራ በማጥናት፣ በዕቅድ በማዘጋጀትና በጀት ይዞ በማስፈቀድ ሠራተኞቹ አስፈላጊውን ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ማዕከሉም ለሠራተኛው የሚያስፈልገውን የልማት ስራ በዕቅድ ይዞ በማስፈቀድ ሠራተኞች አስፈላጊውን ሥልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ አለበት፡፡

ስለሆነም ማዕከሉ የተለያዩ አጫጭርና የረጅም ጊዜ ትምህርትና ሥልጠና በአገርውስጥና በውጪ አገር ሥልጠናና ትምህርት ሰልጣኞችን ግልጽና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በተጠያቂነት አወዳድሮ ለመመልመል/መምረጥ ወጥና ወቅታዊ አፈፃፀም መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም በማዕከሉ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሠራተኞችና አመራሮች የሥራ ኃላፊነታቸውንና ጊዜው የሚጠይቀውን ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙ ለማድረግ ይህ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ

FDRE Education and Training Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration