ሀገራችን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መለያ የሆኑ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ናት፡፡ እነዚህም ቅርሶች የማንነትና የአብሮነት ማገለጭዎች በመሆናቸው በአግባቡ ተጠብቀውና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረከቱና ለቀጣዩ ትወልድ እንዲተላለፉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ይህን ለማሳካት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 209/92 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ ፩ ከተሰጡት ሥልጠና ተግባር አንዱ የሀገሪቱን ቅርሶችን መመዝገብ ነው፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ ወጥና ደረጃውን የጠበቀ የቅርስ ምዝገባ ሥርዓት ባለመኖሩ የሀገራችን ቅርሶች ብዛት፣ አይነትና ስርጭት አይታወቅም ፡ ባለስልጣኑ በክልሎች በተበታተነ የቅርስ ምዝገባ የተከናወነ ቢሆንም ሀገራችን ካላት ሰፊ የቅርስ ሀብት አንጻር እስካሁን ወጥ በሆነ የቅርስ አመዘጋገብ ቅርሶች ተመዝግበወና መረጃዎች በማዕከል ደረጃ የተደራጁበት ሁኔታ ደረጃወን የጠበቀ የቅርስ ምዝገባ ሥርዓት በማፈን ቅርሶች ተመዝግበው እንዲወሉ ለማድረግ ይህ የስራ መመሪያ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
ስለሆነም ወጥና ታውቀውና ከጥፋት ተጠበቀው ለልማት እንዲሁም ግዝፈት የሌላቸወን ይህ የስራ መመሪያ ግዙፍነት ያላቸው የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ለመዝገብ የተዘጋጀ ሲሆን የኢንታንጄብል ባህላዊ ቅርሶችን በተመለከተ በ2002 በባለስልጣኑ የተዘጋጁ የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶች ኢንቨንቶሪ ማንዋል ከዚህ መመሪያ ጋር አብሮ ተግባራዊ ይኖናል፡፡ አንድ የቅርስ መዝጋቢ ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት ሊያውቀው የሚገባ ሰነድ ነው። የመመሪያው የመጀመሪያ ክፍል የቅርስ ምድቦችን ያካተተ ሲሆን፣ ሁለተኛው ክፍልም ስለ ቅርስ ምዝገባ ዓላማ አመዘጋገብ ዘዴዎችና ሂደቶች ሊያስገነዝቡ የሚሉ ሃሳቦችን ይዟል፡፡
ሦስተኛው ክፍል የሚንቀሳቀሱ ቅርሶችን በቅፅ ዐ1 ለመዝገብ የሚረዳ መመሪያን የያዘ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ቅጹ ተራ ቁጥር ከሥራ መመሪያው ተራ ቁጥር ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ መዝጋቢው በሚፈልገው ቦታ ላይ በቀላሉ በዚያዉ ተራ ቁጥር ማበራሪያ ሊያገኝ ይችላል፡፡
አራተኛው ክፍል የሚንቀሳቀሡ ቅርሶችን ለመዘገብ የሚያስችልና ቅፅ ዐ 2 ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ መመሪያ ሲሆን እንደ ክፍል ሦስት የቁጥር ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ ለማወቅ ያስችላል፡፡ የማንቀሳቀሡ ቅርሶችን ባህሪያት መመያው የመጨረሻ ክፍል የቅርስ ምዝገባው በግልና በጋራ ከተለያዩ በስራ ከሚያገናኛቸው አካላት ጋር ሊኖረው ስለሚገባ ስነምግባር የሚስረዳ የአፈጻጸም መመሪያን የያዘ ነው።