የሀገራችን ቅርሶች ለተጨማሪ ሳይንሳዊ ጥናትና ተያያዥ ተግባሮች በአዋጅ ቁጥር 209/1992 አንቀጽ 27 መሠረት ከሀገር የሚወጡበትን ሂደት መቆጣጠርና በዚህም የሚገኘውን ጥቅም ማሳደግ በማስፈለጉ፣
በተለያዩ ጊዜያቶች ከደንበኞች ተመራማሪዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በሙሉ በመመለስ ከተቋሙ የሚያገኙት አገልግሎት ፍትሃዊ እና ምቹ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፣
በዘርፉ ሀገራችንን ለማሳደግና ብሎም ለኢኮኖሚያዊ ግንባታ የሚጠበቅብንን ድርሻ በብቃት ለመወጣት አስተማማኝ መሠረት መዘርጋት ተገቢ በመሆኑ፣
የቅርስ እንክብካቤ ቤተ ሙከራው በቀጣይ በአፍሪካ ብሎም በአለም ላይ ዋና የምርምር እና ልሕቀት ማዕከል እና ከአቻ አህጉራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ የምርምር ተቋማት ይበልጥ ተመራማሪዎችን እንዲስብ ማድረግ ስለሚያስፈልግ፣
ለተገልጋዮች ቀልጣፋ፣ወጪ ቆጣቢና ተጠያቂነት ያለበት አሠራር ማስፈን አስፈላጊ በመሆኑ፣
ስለቅርስ ጥናትና አጠባበቅ በወጣው አዋጅ ቁጥር 209/1992 አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት የሚከተለው መመሪያ ወጥቷል፡፡