የመመሪያ መለያ: 315/2013
ቀን: ታህሳስ 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የዕቃ ማስተላለፍና ተዛማጅ የባህር ወደብ አገልግሎት ስለማስፈጸም የወጣ መመሪያ ቁጥር 315/2013

አገራችን እ.ኤ.አ አፕሪል 13/2002 ከጅቡቲ መንግሥት ጋር በወደብ አጠቃቀም ዙሪያ በፈረመችው ስምምነት መሠረት የጅቡቲ የባህር ወደብ የአገሪቷ ዋነኛ የገቢና የወጪ ዕቃ መነሻና መድረሻ በማድረግ ላለፉት በርካታ ዓመታት እየተገለገለች መሆኗ ይታወቃል፡፡

በሁለቱ አገራት የተፈረመውም የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ስምንት ክፍሎች የያዘ ሲሆን በዋናነት አገሮቹ ያላቸው መብቶችና ተነፃፃሪ ግዴታዎችን ያካተተ ነው፡፡በስምምነቱ ክፍል ሁለት አንቀጽ 5 /4/ መሠረት በጅቡቲ ወደብ ለተሰጠ የዕቃ ማስተላለፍ አገልግሎት ያገኘው የኢትዮጵያ ዕቃ አስተላላፊ ለተሰጠዉ አገልግሎት የወጣዉን ወጪ እና የተሰጠውን አገልግሎት ዝርዝር የሚያሳይ በሁለቱም ወገን የታመነበት የዕቃ ማስተላለፍ አገልግሎት ኢንቮይስ /Invoice ከጅቡቲ ዕቃ አስተላላፊ ትራንዚተር/ በደረሰው በ15 ቀን ውስጥ አገልግሎቱን ለሰጠው የጅቡቲ ዕቃ አስተላላፊ ክፍያን እንደሚፈጽም / The Ethiopia side has agreed to effect the payment for the service provided by the Djibouti maritime transport auxillaries with in 15 days after the submission of the appropriate document/ በሚልበግልፅ አስቀምጧል፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰዉ ይህ የድህረ ክፍያ ሥርዓት በሁለቱ አገራት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ላይ በግልጽ የተቀመጠ ቢሆንም የሁለቱ አገራት ዕቃ አስተላላፊዎች በሚፈጽሙት የሥራ ውል መሠረት የጅቡቲ ዕቃ አስተላላፊዎች ለኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸው እስከ 90 ቀን ድረስ ሊደርስ የሚችል የዱቤ አገልግሎት እየሰጧቸው እንደሆነ ያለዉ የሥራ ልምድ ያሳያል፡፡

ይህ የዱቤ አገልግሎት በተዋዋዮች ነፃ ፍላጎት ላይ የተመሰረተና ለሁለቱም አገራት ዕቃ አስተላላፊዎች ሥራን ከመፍጠር፣ደንበኛን ከማብዛት እንዲሁም ገንዘብን ከማንቀሳቀስ አኳያ ጥቅም ያለው ነው፡፡ ሆኖም ለተሰጠው ዕቃ ማስተላለፍ የዱቤ አገልግሎት ክፍያ በጅቡቲ ዕቃ አስተላላፊና በኢትዮጵያ ዕቃ አስተላላፊ ፍላጎት መሠረት በዉሉ በተጠቀሰው ጊዜ እየተፈጸመ አይደለም፡፡ እንዲሁም የጅቡቲ ዕቃ አስተላላፊዎች በድንበር ዘለል የዕቃ ማስተላለፍ ሥራ ላይ ለመሠማራትና ለመሥራት ፍቃድ ካልተሰጣቸው ከኢትዮጵያ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አስፈፃሚዎች ጋር የሥራ ውል ገብተው መሥራታቸው የአገልግሎት ክፍያቸዉ አሰጣጥ
በተመለከተ ህጋዊ በሆነ መንገድ አለመፈፀሙ ሁለቱ አገራት የተስማሙበትን የድህረ ዕቃ ማስተላላፍ አገልግሎት ክፍያ ስምምነትን ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በጅቡቲ ወገን እ.ኤ.አ ኖቬምበር 25/2013 የጅቡቲ ወደብ ባለሥልጣን ለኢትጵያ ማሪታይም ጉዳይ ባለሥልጣን በፃፈው ደብዳቤ በጅቡቲ ዕቃ አስተላላፊዎች ለኢትዮጵያ ዕቃ አስተላላፊዎች የሚሰጠው የዕቃ ማስተላላፍ ክፍያ በሁለቱ አገራት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ላይ በተገለፀው ቀን ውስጥ እየተከፈለ እንዳልሆነ ገልጿል።

በመሆኑም ቀድሞ የነበረውን የድህረ የትራንዚት አገልግሎት ክፍያን ወደ ቀድመ የትራንዚት አገልግሎት ክፍያ ሥርዓት የሚለወጥ መመሪያ በማዉጣት ተግባር ላይ እንዲውል የተወሰነ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ይሁን እንጂ በጅቡቲ ወደብ ባለሥልጣን የአከፋፈል ሥርዓቱ የተለወጠበት አካሄድ የሁለቱ አገራትን የወደብ አጠቃቀም ስምምነትን ማሻሻል በተፈለገ ጊዜ መከተል የሚገባን ሥርዓትን ያልተከተለ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አገራት በትራንስፖርት ሚኒስትር የሚመራ የልዑካን ቡድን ከሚመለከታቸው የጅቡቲ ወገን ጋር ጅቡቲ ላይ ተገናኝተው የወደብ አጠቃቀም ስምምነቱን በአግባቡ ሊተገበር የሚችልበትን ሥርዓት በመዘርጋት ችግሩን ለማስወገድና በሁለቱ አገራት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት እንቀጽ 5 /4/ ላይ የተገለፀው የድህረ ክፍያ አገልግሎት እንዲቀጥል በጋራ ለመሠራት ስምምነቱ ላይ ደርሰዋል፡፡

በጋራ ስምምነቱ መሠረት የዕቃ ማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ በወደብ አጠቃቀም ስምምነቱ በተጠቀሰዉ ጊዜ መክፈል ከማስቻል በዘለለ ወደፊት እንዲህ ዓይነቱ ችግር እንዳይከሰት የወደብ አጠቃቀም ስምምነቱን በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችል ሥርዓትን መዘርጋት አስፈልጓል፡፡ በመሆኑም ሥርዓቱን ለመዘርጋት የሚያስችሉ የተለያዩ የዳሰሳ ጥናቶች ተደርገው በሁለቱ አገራት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት መሠረት የዕቃ ማስተላለፍ አገልግሎት እናተዛማጅ የባሕር ወደብ አገልግሎት ክፍያን ተግባራዊ ለማድረግና የሚመለከታቸው አካላትን ኃላፊነትና ተግባር ለመወሰን የሚያስችል አገራዊ መመሪያ በማሪታይም ዘርፍ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 549/1999 አንቀጽ 18/ለ/ ላይ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ትራንስፖርት ሚኒስቴር ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር

FDRE Ministry of Transport

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration