ታክስ ከፋዮች በታክስ ውሳኔ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉበት ተደራሽነት ያለው፣ በአግባቡ የተደራጀ፣ የተቀላጠፈና ፍትሃዊ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርብ የታክስ የቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት በማደራጀት የታክስ ከፋዮችን ቅሬታ ለመፍታት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በታክስ ውሳኔ ላይ ቅሬታዎች የሚታዩበትን የቅሬታ አቀራረብና ምርመራ እንዲሁም የውሳኔ ሃሳብ አቀራረብና የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት እና የቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት ሥልጣንና ተግባር ለመወስን የወጣውን መመሪያ ማሻሻል በማስፈለጉ እንዲሁም በሚንስትር መ/ቤቱ ከተደረገው ተቋማዊ የአደረጃጀት ለውጥ ጋር የተጣጣመ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በፌዴራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡