የመመሪያ መለያ: 49/2013
ቀን: ሚያዚያ 29፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የሌበር አታሼ ተግባር፣ ኃላፊነት እና አሠራርን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 49/2013

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅም እንዲጠበቅ የማድረግ እና የኢትዮጵያ ሚስዮኖችን የማስተባበር እንዲሁም የመቆጣጠር ኃላፊነት በውጭ ግንኙነት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 790/2005 አንቀጽ 3(4) እንዲሁም የፌደራል መንግሥት አስፋጻሚ አካላትን ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1097/2011 አንቀጽ 13(10 እና 13) የተሰጠው በመሆኑ፤

በውጭ አገር የስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 አንቀጽ 14(1) የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመመካከር እና መንግሥትን በማስፈቀድ ሌበር አታሼ በሠራተኛ ተቀባይ አገር በሚገኘው ሚሲዮን እንዲመደብ የማድረግ ኃላፊነት የተሰጠው በመሆኑ፤

ኢትዮጵያውያን በዉጭ አገር ለስራ በሚሰማሩባቸዉ አገራት በሚደረገው የሌበር አታሼ ምደባ እና አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቅንጅት ግልጽ፣ ወጥ እና ተቋማዊ በሆነ አሠራር ተግባራዊ የሚደረግበትን ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

አዋጅ ቁጥር 923/2008 አንቀጽ 14(2) የሌበር አታሼ ተግባርና ኃላፊነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ በሚያወጡት የአሠራር መመሪያ እንደሚወሰን የደነገገ በመሆኑ ይህ መመሪያ ወጥቷል

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

Ministry of Labor and Social Affairs

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration