መመሪያ ቁጥር 28/2013
በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማኀበራት አዋጅ 621/2001 ከ አንቀጽ 98- 101 ስለ ህዝባዊ መዋጮ የተደነገገውን በስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ዝርዝር መመሪያ የማዘጋጀቱ አስፈላጊነት ስለታመነበት፤
በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት የሀገር ውስጥ የገቢ ምንጫቸውን ለማሳደግ ህዝባዊ መዋጮ የሚያከናውኑበትን መንገድ ማመቻቸት እንዲሁም ህዝባዊ መዋጮ የማሰባሰቡን ሂደት ግልጽ እና ሐላፊነት የተሞላበት መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ የሂደቱን ዝርዝር ሁኔታ መወሰን በማስፈለጉ፤
የኢፌድሪ በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 621/2001 አንቀጽ 9/4/ እና ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባና አስተዳደር በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 34 መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡