የመመሪያ መለያ: 45/2013
ቀን: ጥቅምት 30፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በአገር ውስጥ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ስለሚሰጥበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 45/2013

የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሕግና አሠራርን በመከተል ፍትሃዊ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የሥራ ስምሪት አገልግሎት በሀገር ውስጥ የሚሰጡበትን ሁኔታ መወሰን በማስፈለጉ፣

በኤጀንሲ አማካኝነት ለሥራ የተሰማራውን ሠራተኛ መብትና ደኅንነት በማስጠበቅ ረገድ ኤጀንሲው እና የአገልግሎት ተጠቃሚው ድርጅት ሊኖራቸው የሚገባውን የጋራና የተናጠል ኃላፊነት ለይቶ የማመልከቱ ተገቢነት ስለታመነበት፣

መንግሥት በሀገር ውስጥ በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚሰጠውን የሥራ ስምሪት አገልግሎት በብቃትና በተገቢው በመከታተል፣ በመቆጣጠርና በመደገፍ፣ በሥራ ላይ የሚሠማሩ ሠራተኞች መብት፣ ደኅንነትና ጥቅም የሚጠበቅበትን ሁኔታ መፍጠር እና የኢንዱስትሪ ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ የሚሰጡ የሥራ ስምሪት አገልግሎቶች በተቀናጀ አግባብ የሚፈጸሙበትን ሁኔታ በመፍጠር ለሀገሪቱ የሥራ ገበያ እድገትና ውጤታማነት ተገቢውን አስተዋጽኦ ማበርከት በማስፈለጉ፤

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአንቀጽ 171/1/ተ እና በአንቀጽ 174 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

Ministry of Labor and Social Affairs

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration