የጂኦስፓሻል ኢንፎርማሽን ኢንስቲትዩት ተልዕኮ ደረጃቸውንና ወቅታቸውን የጠበቁና የተጠቃሚውን ፍላጎት የሚያረኩ መሠረታዊ የምድር መረጃ ማምረት፣ ማሰራጨትና ማማከር እንዲሁም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩትንና የሚሰማሩትን ባለመያዎችና ድርጅቶች የሚያመርቱትን የምድር መረጃ ጥራትና ደረጃ በመቆጣጠርና በዘርፉ የመሪነት ሚና በመጫወት ለሃገራችን ዘላቂ ልማት የበከሉን አስተዋጽኦ ማድረግ በመሆኑ፤
የምድር መረጃ /Geospatial Information/ የማምረት፣ የማሰራጨትና የማማከር ሥራ፤ በዘርፉ የሰለጠነ ባለሞያ፣ መሳሪያና ካፒታል የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ ለአገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የሚጫወተው ሜና ከፍተኛ በመሆኑ ለልማት ስራ እንዲውል ምቹ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በምድር መረጃ /Geospatial Information/ ማምረት፣ ማሰራትና ማማከር የሚሰሩ ባለመያዎች ሞያዊ ብቃት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም በመስኩ ለሚሰማሩ ድርጅቶች በቂ የባለመያ ስብጥርና ስራውን ለማከናወን የሚያስችል አስፈላጊ መሳሪያ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ የሕዝብንና የመንግሥትን ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፤
ከዚህ በተጨማሪም የምድር መረጃ /Geospatial Information/ ምርት ማምረቻ መሳሪያ አስምጪና ላኪ ድርጅቶች የማያስመጧቸውንና የሚልኳቸው መሣሪያዎች ጥራትና ደረጃቸወን የጠበቁ መሆናቸወን መከታተልና መቆጣጠር እንዳለበት በኢንስቲትዩቱ በኩል ስለታመነበት፤
ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በዘርፉ የተሰሩትን ባለሞያዎችና ድርጅቶች ከስራ ጥራትና ብቃት አንፃር ለመቆጣጠር የሚያስችል መመዘኛ መስፈርት መኖር ያለበት በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርማሸን ኢንስቲትዩት በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1079/2010 በሃገሪቱ ወስጥ የሚመረቱ የምድር መረጃ /Geospatial Information/ ምርቶችን የመቆጣጠር ሥልጣን የተሰጠው ከመሆኑም ባሻገር በንግድ ምዝገባና ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 42 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሞያው ለሚሰማ ባለመያዎችና ድርጅቶች የትምህርት ዝግጅታቸውን፣ የስራ ልምዳቸውን፣ ለስራው የሚያስፈልጋቸውን መሳሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ግብዓቶችን ማሟላታቸውን በማጣራት እና በዘርፉ ለተሰሩት አስሜዎችም ሆነ ላኪዎች የሞያ ብቃት ማረጋገጫ በመስጠት ወደ ሥራ እንዲገቡና ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የምድር መረጃ ለተጠቃሚው የሚያቀርቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይህንን መመሪያ አዘጋጅቷል፡ ፡