እያደገ የመጣውን ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት እንዲቀንስ ብሎም ለህብረተሰቡ በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ፤ ሀገራችን ለጊዜው የገጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት በመቋቋም መረታዊ የምግብ ሸቀጦች እና የኢንዳስትሪ ግብዓቶችን ከውጭ በልዩ ሁኔታ ለማስገባትና ለማጫረት እንዲያስችል በማሰብ የጠቅላይ ሚስትር ጽ/ቤት የውጭ አቅራቢዎች ከራሳቸው የውጭ ምንዛርሬ ምንጭ በመንግሥት የተለዩ እና የሚለዩ ሸቀጦችንና የኢንዳስትሪ ግብዓቶችን ወደ አገር ወስጥ ለማስገባት እንዲችሉ የገንዘብ ሚስቴር መማሪያ እንዲያወጣ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ/ም በቁጥር 05/732 በተፃፈ ደብዳቤ ወክልና የሰጠ በመሆኑ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር ይህን መመሪያ አውጥቷል።