የመመሪያ መለያ: 398/2013
ቀን: ጥቅምት 25፥ 2007 ዓ.ም.
Language: Amharic

በፀሀፊነት ሴክሬታሪ የሥራ መደቦች ሲያገለግሉ ቆይተው የትምህርት ደረጃቸውን በዲግሪ ደረጃ ያሻሻሉ ሰራተኞች የስራ ልምድ አያያዝን በተመለከተ የወጣ መመሪያ ቁጥር 398/2013

አገራችን በሁሉም መስኮች በከፍተኛ የዕድገትና የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በተለይም የትምህርትን ለሁሉም ተደራሽነትን በማስፋትና የቅበላ አቅምን በማሳደግ ለዘመናት ትምህርት ማግኘት የጥቂቶች መብት የሆነበትን ሥርዓት ከመሠረቱ በመቀየር በትምህርቱ ዘርፍ የታየው እመርታ የሌሎች ዕድገቶቻችን ጠንካራ መሠረት እየሆነ መምጣቱ በገሀድ የሚታይ እውነታ ሆኗል፡፡

በተለይም ሁለትና ሶስት ይቆጠሩ የነበሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሰላሳ በላይ ቁጥራቸው እንዲጨምር በመደረጉ ቀደም ሲል ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት በላይ ዕድል ማግኘት ያልቻሉና በዚሁ ደረጃ ወደ ሥራ ዓለም የተቀላቀሉ የሲቪል ሰርቪሱ አባላት አጋጣሚውን በመጠቀም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች እየተመረቁ በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በተለይ በጽህፈት ሥራ ላይ የተሰማሩ በአብዛኛው ሴት እህቶቻችን ዕድሉን በሰፊው እየተጠቀሙበት ቢገኙም በፀሀፊነት ያገለገሉበትን የሥራ ልምድ ከሌሎች የሥራ ዘርፎች ጋር አግባብነቱን አረጋግጦ የሰጡት አገልግሎት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ካመጡት የትምህርት ማስረጃ ጋር በማጣመር ከፍ ባሉ የፕሮፌሽናል የሥራ መደቦች ላይ እንዲመደቡበት ማድረግ አለመቻሉ የሠራተኞቹ የቅሬታ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ይህንኑ ሁኔታ ለመለወጥና ሠራተኞቹም ለረዥም ጊዜ የሰጡትን አገልግሉት ዋጋ ማሳጣት አግባብ ሆኖ ባለመገኘቱ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ይህን መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የህዝብ አገልግሎት እና የሰው ሀብት ሚኒስቴር

Ministry of Public Service and Human Resources

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration