የመመሪያ መለያ: 500/2013
ቀን: ጥቅምት 1፥ 2006 ዓ.ም.
Language: Amharic

የውሃ ነክ ሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና ባለሙያዎች ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥን በሚመለከት የወጣ መመሪያ ቁጥር 500/2013

የውሃ ነክ ሥራ ጥናት፣ ዲዛይን፣ ግንባታና ቁጥጥር በዘርፉ የሰለጠነ ባለሙያ፣ መሣሪያና ካፒታል የሚጠይቅ የሥራ መስክ ከመሆኑም በላይ የውሃ ሀብታችን ለልማት እንዲውል በማስቻል ረገድ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣

በውሃ ነክ ሥራዎች የሚሰማሩ ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም በመስኩ የተሰማሩ፣ ተቋራጭና አማካሪ ድርጅቶች በቂ የባለሙያ ስብጥርና ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል አስፈላጊ መሳሪያዎች ያላቸው ወይም ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ማረጋገጥ የሕዝብንና የመንግሥትን ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፤

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በዘርፉ የተሰማሩትን ባለሙያዎች ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች ከሥራ ጥራትና ብቃት አንፃር መቆጣጠር የሚያስችል መመዘኛ መስፈርት መኖር ያለበት በመሆኑ፣

የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 197/1992 በአንቀጽ 31 እና በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር ደንብ ቁጥር 115/1997 አንቀጽ 20 እና 21 መሠረት ይህንን መመሪያ እውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር

Ministry of Water, Irrigation and Electricity

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration