የመመሪያ መለያ: 465/2013
ቀን: የካቲት 1፥ 2010 ዓ.ም.
Language: Amharic

የጥራት መስፈርቶችን ስለማያሟላ የዕፅዋት ዘር አጠቃቀም እና አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 465/2013

በአገሪቱ የዘር ጥራትን በማረጋገጥ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለሁለት ተከታታይ አሥርት ዓመታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ጥረት መካከል የሚጠቀሰው ዘር በማምረት ሂደት በማሳና በላቦራቶሪ የሚካሄደው የዘር ጥራት ቁጥጥር አንዱ ነው፡፡ ይህንንም ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ፌደራልና ክልሎች ከፍተኛ በጀት በመመደብ ስራውን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡

ከዓመታዊ በጀታቸዉመ ከፍተኛ ካፒታል በመመደብ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርት መሠረት በመስክ ነዉ ጥራት ቁጥጥር ሥራ በመሥራት ያለፉና የወደቁ ማሳዎችን በመለየት ካለፉ ማሳዎች የተሰበሰበ ዘር ለቀጣይ የዘር ጥራት ፍተሻ ሲያዘጋጁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ የወደቁ ማሳዎችንም መውደቃቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት ለአምራቾችና ለሚመለከታቸው የዘር ጥራት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ሁሉ በሪፖርት የማሳወቅ ሥራ ይሠራል፡፡ የመሰክ የጥራት ቁጥጥር መስፈርት አሟልቶ ካለፉና ተበጥሮ ከተዘጋጀ የዘር ሎት ናሙና በመውሰድ በላቦራቶሪ ደረጃ ፍተሻ በማካሄድ የዘር ጥራትን በማረጋገጥ ለወደቁ ሎቶች መውደቃቸውን የሚገልጽ ሪፖርት ለአምራቾች ይቀርባል፡፡ ይህ ሁሉ ጥረት ቢደረግም ለወደቁ ማሳዎችና ሎቶች ከስርጭቱ ስለመወገዳቸው የሚገልጽ ሪፖርት ከመጻፍ ባለፈ ከወደቁ ማሳዎች የተገኘውን ዘርና የወደቁ ሎቶች ከግብይት ሥርዓቱ መወገዱን የሚያረጋግጥ አሠራር ስላልነበረ ችግሩን በተግባር ለመፍታት ይህንን መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የግብርና ሚኒስቴር

Ministry of Agriculture

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration