የመመሪያ መለያ: 12/2012
ቀን: ነሀሴ 7፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የመኖ አምራች አስመጪ ጅምላ አከፋፋይና ላኪ ድርጅቶች የምዝገባና የሥራ ፈቃድ መስጫ አሠራር መመሪያ ቁጥር 12/2012

በእንስሳት መኖ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩና የሚሰማሩ ድርጅቶች የሚያመርቱትን፣ ከዉጭ ወደ ሀገር የሚያስገቡትን፣ ሚያከፋፍሉትን ወይም ከሀገር ወደ ዉጭ የሚልኩትን የመኖጥራትና ደኅንነት በማረጋገጥ የቀጥተኛ ተመጋቢዉን እንስሳ እንዲሁም የእንስሳት ምርት ተጠቃሚዉን ህብረተሰብ ጤና መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ወደ ሀገር የሚገባ መኖ እና መኖ ግብዓት ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠና አስፈላጊ መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በእንስሳት መኖ ላይ በቂና ሕጋዊ ቁጥጥር ለማካሄድ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

በመኖ ንግድ ሥራ ላይ ለሚሰማራ ማንኛውም ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠት፣ መከታተልና መቆጣጠር አስፈላጊ የንግድ አሠራር ሥርዓት ሆኖ በመገኘቱ፤

የመኖ ንግድ ሥራ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሥራዎችን ግልጽና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሠራር ለማካሄድ እንዲቻልና ተገልጋዮችም ይህንን አውቀው መደረግ የሚገባውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት የአገልግሎት ጥያቄአቸውን በአግባቡ እንዲያቀርቡ ለማስቻል፤

በኢትዮጵያ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዋጅ ቁጥር 728/2004 አንቀጽ 28 ንዑስ አንቀጽ 2 ለእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነትመሠረትይህ የመኖ አምራች፣ አስመጪ፣ ጅምላ አከፋፋይና ላኪ ድርጅቶች የምዝገባና ፈቃድ መስጫ አሠራር መመሪያ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የእንስሳት መድኃኒትና የእንስሳት መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን

Veterinary Drug and Animal Feed Administration and Control Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration