የመመሪያ መለያ: 510/2013
ቀን: መጋቢት 1፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የዋና ሥራ አስፈፃሚዎች የምልመላ እና ምደባ ማዕቀፍ መመሪያ ቁጥር 510/2013

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የልማት ድርጅቶችን ውጤታማ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና ኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት፣ መከታተል፣በልማት ድርጅቶችና አክስዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥትን በመወከል የመንግሥት ባለቤትነት መብት ለማስከበርና ለመምራት የተቋቋመ ኤጀንሲ ነው፡፡

ስለሆነም በደንብ ቁጥር 445/2011አንቀጽ 5 ቁጥር 4 መሠረት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተፈላጊ ችሎታ፣ ልምድ እና እውቀት ባላቸው ስራ መሪዎች የሚመሩበትን ስርዓት ለመዘርጋትና ተግባራዊ ለማድረግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በብቃት ሊመሩ የሚችሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች የሚመደቡበትና ኃላፊነታቸን በአግባቡ ሳይወጡ ሲቀሩከሥራ ኃላፊነታቸው የሚነሱበትን እንዲሁም ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ይህን የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አሰፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ሁሉም የልማት ድርጅቶችበየራሳቸው የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ በማዘጋጀት እና በቦርዱ በኩል በማፀደቅ የዋና ሥራ አስፈፃሚው ቅጥርና ምደባ እያከናወኑ የሚገኙ ቢሆንም አካሄዱ በወጥነት አንዲመራ ለማድረግና በሥራ አስፈፃሚ ቅጥርም ሆነ ስንብት ላይ የኤጀንሲው ይሁንታ እንዲሰጥበት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የኤጅንሲውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 445 /2011 አንቀጽ 5 (4 እና 13) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር

Public Enterprises Holding and Administration

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration