በሀገር አቀፍ ደረጃ ጳጉሜ አንድ ቀን የአገልግሎት ቀን ሆኖ እንዲከበር በመንግሥት የተወሰነ በመሆኑ በዕለቱ ለሚከበረው የአገልግሎት ቀን በፌዴራል የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ምስጋና ሊቀርብላቸው የሚገቡ ሠራተኞችን ለይቶ ማበረታታት በማስፈለጉ፣
በመንግሥት መስሪያ ቤት ውስጥ የረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ላገለገሉ ሠራተኞች ግልጽ በሆነ አሠራር ሥርዓት ዕውቅናና ሽልማት መስጠት በማስፈለጉ፤
በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 97 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡