የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና የሚያስከትለው ጉዳት ለመቀነስ ስለ ሚወሰዱ ክልከላዎች እና ግዴታዎች በሕግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመድኃኒትና ምግብ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 72 ንዑስ-አንቀጽ (2)፣ በምግብ፣መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661 አንቀጽ 55 ንዑስ-አንቀጽ (3) እና የምግብ፣ የመደኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 98 መሠረት የሚከተለውን መመሪያአውጥቷል፡፡