- ከመንግስታዊ ስራዎች ጋር ተያይዞ በስትራቴጂያዊ የዕቅድ ዘመን ውስጥ የሚጠበቅ ውጤትን ለማሳካት የተቋም ስትራቴጂዎችን ወደ የዕለት ተዕለት ተግባር መንዝሮ ከሠራተኞች ጋር መግባባትን በመፍጠር፣ የግለሰቦችንና የቡድኖችን አፈጻጸም በማሻሻል የማያቋርጥ ዕድገትን ለማስመዝገብ፣ ለውጤቱ ስኬታማነት የሠራተኞችን አስተዋፅኦ ለመመዘን፣ የሠራተኞችን አቅም በቀጣይነት በመገንባት ለማሳደግና በአጠቃላይ ስራን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችል የአፈጻጸም አመራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣
- የተቋም ዕቅድ ከሀገራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲነሳ ለማድረግ፣ ስትራቴጂዎች ከመነጨ የተቋም
- አፈጻጸምን በተቋም፣ በስራ ሂደትና በፈጻሚ ደረጃ በተናበበ መልኩ ለመገምገምና ለመመዘን እንዲቻል፣
- በአፈጻጸም ምዘና ስርዓቱ ባሕርይን ከዕለት ተዕለት የስራ አፈጻጸም ነጥሎ ሳይሆን ከአፈጻጸም ጋር ያለውን ውሁድ ገፅታውን ተቀብሎ በተያያዥነትና በአግባቡ ለመመዘን እንዲቻል፣
- የለውጥ ሠራዊቱ የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ነጥብ መስጠትን ብቻ ሳይሆን ለነጥብ አሠጣጥ መሠረት የሆነውን መረጃ መያዝን ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ማጠቃለያ – ምዕራፍ ባሉ ሂደቶች የቡድን ሥራ አድርጎ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲተገበር ለማስቻል፣
- የአፈጻጸም ግምገማና ምዘና ከሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች ጋር በቅንጅትና በትስስር የመተግበር አሠራርን ለማጎልበት፣
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር በመንግሥት ሰራኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 31 እና አንቀጽ 32/3 መሠረት በስራ ላይ የነበረውን የሰራተኞች ስራ አፈጻጸም መመሪያ አሻሽሎ አቅርቧል፡፡